Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በብራዚል በኮሮና የተያዙ ሰዎች ቁጥር 5 ሚሊየንን አለፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በብራዚል በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ5 ሚሊየን መብለጡ ተነገረ፡፡

በአለም ኮሮና ከጸናባቸው አገራት መካከል በሶስተኛ ደረጃ የተቀመጠችው ብራዚል በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 5 ሚሊየንን ተሻግሯል፡፡

እስካሁን በአገሪቱ ከ5 ሚሊየን 690 በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ የሟቾች ቁጥር ወደ 150 ሺህ መጠጋቱም ነው የተነገረው፡፡

በፕሬዚዳንት ጄር ቦልሶናሮ ቫይረሱን ለመከላከል በሚደረጉ እርምጃዎች ላይ የባለሙያዎችን ምክር ችላ በማለታቸው ወረርሽኙ ሊስፋፋ እንደቻለ ይነሳል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ወረርሽኙን መከላከል ላይ የሚሰነዘሩ ትችቶችን ውድቅ ቢያደርጉም እንቅስቃሴዎችን መገደብን መቃወም እንዲሁም በኢኮኖሚው ላይ ለማተኮር መወሰኑ በከፍተኛ ሁኔታ ከፋፋይ እንደሆነ ነው የተነገረው ፡፡

እስካሁን በአለም ዙሪያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 36 ሚሊየን 400 ሺህ በላይ ሲሆኑ ህይዎታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 1 ሚሊየን 60 ሺህ በላይ ሆነዋል፡፡

ሆኖም እስካሁን ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ከ27 ሚሊየን 400 ሺህ እንደሚልቅም ነው የተነገረው፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ እና ዎርልድ ኦ ሜትር

Exit mobile version