Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሰበታ ከተማ የተገነባው ዲማ ማኞ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 28 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሰበታ ከተማ የተገነባው ዲማ ማኞአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመርቋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ ትምህርት ቤቱን መርቀዋል።

ከተማ አስተዳደሩ በዘንድሮው በጀት አመት 171 ተጨማሪ ክፍሎች መገንባቱን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ብርሀኑ በቀለ ገልፀዋል።

ትምህርት ቤቶቹ በከተማ አስተዳደሩ እና በባለሀብቶች እንዲሁም በህብረተሰቡ የበጎ ፈቃድ መርሀ ግብር የተገነቡ መሆኑም ተገልጿል።

በዛሬው እለትም በሰበታ ከተማ አስተዳደር ዲማ ማኞ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ግሩፕ የተገነቡ ተጨማሪ ስምንት የማስፋፊያ የመማሪያ ክፍሎች እና ቤተ መጽሃፍት ተመርቀዋል።

ከተማ አስተዳደሩም ለማስፋፊያ ስራዎቹ ከ81 ሚሊየን ብር በላይ መድቦ ሲሰራ መቆየቱም ተነግሯል።

በትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ የተመራ ልዑክ በሰበታ ከተማ አስተዳደር በ2013 በጀት አመት የኮሮና ቫይረስን እየተከላከሉ ትምህርት መጀመር የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት እና የማስፋፊያ ስራዎች እየተጎበኘ ይገኛል።

ልዑኩ ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የተውጣጡ ከፍተኛ አመራሮችን ያቀፈ ነው።

በትዝታ ደሳለኝ

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version