አዲስ አበባ ፣ መስከረም 28 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጂማ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 409 ተማሪዎች በዛሬው እለት አስመረቀ።
ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም በፒ ኤች ዲ የተመረቁ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው በያዝነው ዓመት ቀደም ብሎ ካስመረቃቸው 3 ሺህ 139 ተማሪዎች ጋር በድምሩ 4 ሺህ 548 ተመሪዎችን አስመርቋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀማል አባ ፊጣ፤ ዩኒቨርሲቲው ከሚያከናውናቸው የመማር ማስተማር ተግባራት ጎን ለጎን ኮቪድ 19ኝን ለመከላከል የጀመራቸውን ውጤታማ ጥናቶች እና የፈጠራ ስራዎች አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
የእለቱ የክብር እንግዳ የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት እያጠናቀቀ መሆኑን በመግለፅ ቫይረሱን ለመከላከል ጥረቶች መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ሠላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ለመፍጠር መሠራት እንዳለበት መልክት አስተላልፈዋል፡፡
በአፈወርቅ አለሙ

