አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሽንሌና ቦረና ከርሰ ምድር ውሃ መስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ጥናትና ዝርዝር ዲዛይን እየተካሄደ ይገኛል፡፡
የሽንሌና ቦረና ከርሰ ምድር ውሃ መስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ጥናትና ዝርዝር ዲዛይን ስራዎች ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ስራዎች ኮርፖሬሽን ጋር ውል ተገብቶ ከግንቦት 2012 ዓ.ም ጀምሮ ስራው እየተከናወነ ይገኛል፡፡
የጥናትና ዝርዝር ዲዛይን ስራው በሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሚካሄድና ጥናትና ዝርዝር ዲዛይኑም በ20 ሺህ ሄክታር ላይ የሚከናወን መሆኑም ነው የተነገረው፡፡
የቦረና ከርሰ ምድር ውሃ መስኖ ልማት ፕሮጀክት ጥናትና ዝርዝር ዲዛይን ስራው በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሚካሄድና ጥናትና ዝርዝር ዲዛይኑም በ10 ሺህ ሄክታር ላይ የሚከናወን መሆኑም ተገልጿል፡፡
በፋይናንሺያል ፕሮፖዛል መሰረት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ስራዎች ኮርፖሬሽን አሸናፊ ሆኖ በመመረጡ ከኮርፖሬሽኑ ጋር የስራ ውለታ ውል መገባቱም ነው የተነገረው፡፡
የሽንሌና ቦረና ከርሰ ምድር ውሃ መስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ጥናትና ዝርዝር ዲዛይን ስራዎች እያንዳንዳቸውን በ9 ሚሊየን ብር ወጪ ለመስራት ውል መገባቱም ታውቋል፡፡
የሽንሌና ቦረና ከርሰ ምድር ውሃ መስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ጥናትና ዝርዝር ዲዛይን በኮንትራት ውሉ መሰረት ህዳር ላይ ለማጠናቀቅ ውል የተገባ ሲሆን እስከ 2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ድረስ በቅደም ተከተል 46 እና 43 በመቶ አፈፃፀም ላይ መድረሳቸውን የውሃና መስኖ ኢነርጂ ሚኒስቴር የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ብዙነህ ቶልቻ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

