አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በሶማሌ ክልል የተገነባው የፀሀይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑ ተገለፀ።
በምርቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የሶማሊ ክልል ምክትል ርዕስ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ፣የውሃ፣ መስኖና እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትርን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት እንዲሁም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተርና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
በሶማሌ ክልል ዶሎ ዞን ዳኖድ ወረዳ የተገነባው ይህ የፀሃይ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የማመንጨት አቅሙ 325 ኪሎ ዋት ሲሆን 30 ሚልየን ብር ወጪ መደረጉን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

