አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ2020 የኖቤል የሰላም ሽልማትን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አሸነፈ፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አንዱ አካል የሆነው የዓለም የምግብ ፕሮግራም የዘንድሮውን የሰላም ሽልማት የወሰደው ረሃብን ለመዋጋት ባደረገው ጥረት መሆኑን ኮሚቴው አስታውቋል፡፡
በዚህም የዓለም የምግብ ፕሮግራም ከኮሚቴው 1 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር ተበርክቶለታል፡፡
ፕሮግራሙ ይህንን የኖቤል ሽልማት ሲያሸንፍ 101ኛ ነው ተብሏል፡፡
የፕሮግራሙ ቃል አቀባይ የሽልማቱን ይፋ መሆን ተከትሎ ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡
የዓለም ምግብ ፕሮግራም በ88 ሃገራት ውስጥ የሚገኙ 97 ሚሊየን ሰዎችን እንደሚደግፍ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የባለፈውን ዓመት የኖቤል የሰላም ሽልማት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ማሸነፋቸው የሚታወስ ነው፡፡

