Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ82 ሺህ አለፈ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ24ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 8 ሺህ 24 የላቦራቶሪ ምርመራ 865 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ 9 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
በዚህም በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 82 ሺህ 662 ደርሷል።
በሌላ በኩል 668 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን በዚህም በአጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 37 ሺህ102 መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ያሰፈሩት መረጃ ያመለክታል።
በ24ሰዓት ውስጥ 9 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 1ሺህ 272 ሰዎች በቫይረሱ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
44 ሺህ 287 ሰዎች በአሁን ወቅት ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሲሆን 243 ፅኑ ህሙማን ደግሞ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል ተብሏል።
በኢትዮጵያ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊየን 335ሺህ 856 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።
Exit mobile version