Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

መልካ አቴቴ ኢሬቻ በቡራዩ ከተማ ተከበረ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) መልካ አቴቴ ኢሬቻ በቡራዩ ከተማ ተከበረ፡፡

በበዓሉ ላይ አባ ገዳዎች፣ ሃደ ሲንቄዎች፣ ቄሮወች እና ቀሬዎች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡

በበዓሉ ላይ የተገኙ አባ ገዳዎች የኢሬቻ በዓል የብሄር ብሄረሰቦችን ግንኙነት እንደሚያጠናክር ተናግረዋል፡፡

የበዓሉ ተሳታፊዎች በበኩላቸው መልካ አቴቴ ኢሬቻ የገዳ ተምሳሌትና ፍቅር የሚገለጽበት በዓል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አከባበሩ የጤና ሚኒስቴር የኮቪድ19 ወረርሽኝን ለመከላከል ባስቀመጠው መመሪያ መሰረት ነው የተከበረው፡፡

በኡጋሳ ፉፋ

Exit mobile version