Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደረገ።

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መረጃ፤ ከነገ ጥቅምት 1፣ 2013 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 30፣ 2013 ዓ.ም የሚቆይ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ማድረጉን አስታውቋል።

በዚህም መሰረት በአዲስ አበባ የሚኖረው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በሊትር፤

ቤንዚን 21 ብር ከ87 ሳንቲም፤

ኢታኖል ድብልቅ ቤንዚን 21 ብር ከ33 ሳንቲም፤

ነጭ ናፍጣ እና ኬሮሲን 19 ብር ከ9 ሳንቲም፤

ቀላል ጥቁር ናፍጣ 16 ብር ከ94 ሳንቲም፤

ከባድ ጥቁር ናፍጣ ደግሞ 16 ብር ከ51 ሳንቲም

በማስተካከያው በመስከረም ወር በሊትር በ26 ብር ከ97 ሳንቲም ሲሸጥ የቆየው የአውሮፕላን ነዳጅ የ2 ብር ከ60 ሳንቲም ቅናሽ ተደርጎበት በ24 ብር ከ37 ሳንቲም እንዲሸጥ ተወስኗል።

በዓለም ገበያ ላይ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ እንደአስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊያደርግ እንደሚችልም ነው የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያደረሰን መረጃ የሚያሳየው።

 

 

Exit mobile version