Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፋኦ ከዘጠኝ ሚሊየን በላይ ሱዳናውያን ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተባበሩት መንግስታት የምግብና የእርሻ ድርጅት (ፋኦ) ከዘጠኝ ሚሊየን በላይ ሱዳናውያን ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው አስታወቀ፡፡
ድጋፉ በጎርፍ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የሚያስፈልግ መሆኑንም ነው ያስታወቀው፡፡
እንደ ድርጅቱ ገለፃ በሚሊየን የሚቆጠር ሄክታር የእርሻ መሬት በጎርፉ ምክንያት ጉዳት ደርሶበታል፡፡
በዚህም ሃገሪቱ በሚሊየን ቶን የሚገመት እህል ማጣቷን ድርጅቱ አስፍሯል፡፡
በሱዳን ከሃምሌ ወር ጀምሮ የጣለው የዝናብ መጠን በአስርት አመታት ውስጥ ከታየው እጅግ የከፋው ነው ተብሏል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ዜጎች በተበከለ ውሃ ሳቢያ ለበሽታ ሊዳረጉ ይችላሉም ነው ያለው፡፡
አሁን ላይም በሃገሪቱ የወባ በሽታ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩም ታውቋል፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
Exit mobile version