አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ 3 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የሚገመት ወርቅ ተያዘ፡፡
1 ነጥብ 4 ኪሎ ግራም መጠን ያለው ወርቅ አዲስ አበባ ከሚገኘው የካሜሩን ኤምባሲ ወደ ካሜሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተላከ መልዕክት በማስመሰል ከሀገር ለማስወጣት ሲሞከር በተደረገ ፍተሸ መያዙ ታውቋል፡፡
የተያዘው ወርቅ በወቅታዊ የብሔራዊ ባንክ የመግዣ ዋጋ 3 ሚሊየን 400 ሺህ ብር ግምታዊ ዋጋ እንደወጣለት ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በዚህም የገቢዎች ሚኒስቴር የሀገርን ሀብት ከምዝበራ ለታደጉ የጉምሩክ ሰራተኞች እና የፀጥታ አካላት ምስጋና አቅርቧል፡፡

