አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 3 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሰላም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የቦርድ አባላት ጋር በዛሬው ዕለት ውይይት አካሂዷል።
በውይይቱ ወቅት ሚኒስቴሩ በኢትዮጵያ ሕዝቦች መካከል የቆየውን የመከባበር ባህል አጠናክሮ ለማስቀጠል የእምነት ተቋማት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጿል።
በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ ዳይሬክተር ጄኔራል ወይዘሮ አስማ ረዲ÷ የውይይት መድረኩ ከእምነት ተቋማት ጋር ለሚከናወኑ ተግባራት የጋራ መግባባት ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።
የሰላም ሚኒስቴር በቀጣይም ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሚገኙ የእምነት ተቋማት ጋር ለሚያካሂደው የምክክር መድረክ በተዘጋጀው የጋራ ዕቅድ ላይ ውይይት ማድረጉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

