Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ፡፡
ፕሬዚዳንቷ የሴራሊዮን አምባሳደር አብዴኩንሌ ጆሊፍ ሚልተን ኪንግ፣ የአየርላንድ አምባሳደር ኒኮላ አን ብሬናን፣ የኔዘርላንድስ አምባሳደር ሄንክ ያን ቤከር፣ የፊንላንድ አምባሳደር ኡቲ ሆሎፓይነን፣ የስዊድን አምባሳደር ሃንስ ሄንሪ ሉንድክቪስት እና የፖላንድ አምባሳደር ፕርዜኒስላው ቦባክን የሹመት ደብዳቤ መቀበላቸው ታውቋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የስፔን አምባሳደር ማኑኤል ሳላዛር ፓልማ፣ የፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማሬሾ እና የካሜሩን አምባሳደር ኤውምብዌ ሞኖኖ ቸርችልን የሹመት ደብዳቤ ተቀብለዋል፡፡
አምባሳደሮቹ በበኩላቸው በየሀገሮቻቸውና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት የበለጠ እንዲጠናከር ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ መናገራቸውን ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
Exit mobile version