አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቦርድ በትናትናው ዕለት ለሶስት ምሁራን የፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን አስታወቀ።
በዚህም ዩኒቨርሲቲው ለዶክተር ታደሰ አወቀ ፣ ለዶክተር የማታው ወንዴ እና ለዶክተር አሰግድ ደምሴ ሙሉ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል።
ዩኒቨርሲቲው በፌስቡክ ገፁ ባወጣው ፅሁፍ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ለተሰጣቸው ምሁራን የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

