አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 4 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሁለተኛው ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመደገፍ እንዲሁም ተያያዥ የፋይናንስና የኢኮኖሚ ወንጀሎች ጥናት በይፋ ተከፍቷል።
የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ዝግጅቱን በይፋ ሲከፍቱ÷ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ወደ ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ስርዓት ለመግባት እየተዘጋጀች ባለችበት ወቅት የዓለም ባንክ እያበረከተ ላለው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።
የዓለም ባንክ ግሩፕ የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ የገንዘብ ወንጀልን በብቃት ለመቋቋም የሚያስችል ጠንካራ ስርዓት ለመዘርጋት በምታደርገው ጥረት ተቋማቸው አጋር ሆኖ እንደሚቀጥል መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

