አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 5 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቀጣይ አስር አመታት የከተማ ነዋሪዎችን ህይወት ለማሻሻል የሚረዱ ስራዎች እንደሚከናወኑ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አስታወቀ።
የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሴክተር የቀጣይ 10 ዓመታት መሪ ዕቅድ ትግበራ ማስጀመሪያ ጉባኤ ዛሬ በአዳማ ከተማ ተጀምሯል።
“የብልፅግና ማዕከላት ከተሞች እና ተወዳዳሪ የኮንስትራክሽን እንዱስትሪን ለመገንባት በጋራ እንሰራልን” በሚል መሪ ቃል በሚካሔደው በዚህ ጉባኤ ላይ ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሀመድ እንደተናገሩት÷ መሪ እቅዱ የከተማ ህዝብ ዕድገት በጥንቃቄ ለመምራት የሚያስችል ነው ብለዋል።
በከተሞች የዜጎች ህይወት የሚለወጥበት ለማድረግ፣ የተሻለ ለውጥና ዕድገት ለማስመዝገብ የሚረዱ ስራዎች ይከናወናሉ ብለዋል።
ዕቅዱ በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሴክተሮች እመርታዊ ለውጥ ያመጣልያሉት ሚኒስትሯ÷ በተለይ ዘመናዊ የመሬት አስተዳደር፣ፅዱና አረንጓዴነት፣የስራ ዕድል ፈጠራ የቤቶች ልማትና የኮንስትራክሽን ሴክተር በዕቅዱ በቅድሚያ ትኩረት የተሰጠበት ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በበኩላቸው÷ ከተሞችን በቴክኖሎጂና በዕውቀት በማልማት ስራ አጥነትን በሚፈለገው ደረጃ መቀነስ እንደሚቻል ተናግረዋል።
የከተማ ግብርናን ጨምሮ በሁሉም የመሰረተ ልማት ዘርፎች ላይ በማሳተፍ በዜጎች ህይወት ላይ ለውጥ ማምጣትና ገቢን ማሳደግ እንደሚገባም አመላክተዋል።
የአስር ዓመት መሪ ዕቅዱም በሀገሪቱ የከተሞች ልማት ላይ መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት በሚችል መልኩ በጥብቅ ስነ ምግባር እንደሚተገበር ያላቸውን እምነት ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
0
People Reached
0
Engagements
Boost Unavailable
Like
Comment
Share

