አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 5 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ 2013 ዓ.ም 343 ሺህ ዩኒት ደም ለመሠብሠብ መታቀዱን የብሄራዊ ደም ባንክ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ታየ ገለጹ።
ለሶስት ቀናት የሚቆይ 8ኛው ሃገር አቀፍ የብሄራዊ ደም ባንክ የምክክር መድረክ በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
የብሄራዊ ደም ባንክ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ታየ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ÷ባለፈው የበጀት አመት በሀገሪቱ ባሉ 43 የደም ባንኮች 310 ሺህ ዩኒት ደም ለመሠብሠብ ታቅዶ 288 ሺህ 966 ዩኒት ደም መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል።
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በደም መሠብሠቡ ላይ ተፅዕኖ ፈጥሮ የነበረ ቢሆንም በሀገር አቀፍ ደረጃ በጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች ባደረጉት ርብርብ የዕቅዱ 93 በመቶ ተሳክቷልም ነው ያሉት ።
ደም ለጋሾችን ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመጠበቅ አዲስ የ መረጃ አያያዝ ስርዓት መዘርጋቱን አስታውቀዋል።
በኤልያስ አንሙት
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

