አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ በኢትዮጵያ ከሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌት ተረኪን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በሁለቱ ሀገራት መካከል ባለው የጋራ ኮሚሽን ጉዳይ እና በዚህ ዓመት በኢትዮጵያ በሚካሄደው የሃገራቱ የጋራ ኮሚሽን ሁኔታና ስለሚከናወኑ ተግባራት ምክክር አድርገዋል፡፡
በተጨማሪም በሩሲያ መንግስት በሚሰጡ የነፃ ትምህርት እድሎች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌት ተረኪን ሩሲያ ለትምህርት ዘርፉ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥልም ተናግረዋል፡፡

