Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የትምህርት ቤት አመራሮችን አቅም ለማሳደግ የስልጠና ማንዋል ተዘጋጅቷል -ትምህርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 12 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮች የስልጠና ሂደት ለማሻሻል የሚያስችሉ የማሰልጠኛ ማንዋሎች መዘጋጀታቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የማሰልጠኛ ማንዋሉ ትምህርት ሚኒስቴር ከኤጁኬሽን ደቨሎፕመንት ትረስት ከተሰኘ ድርጅት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው ተብሏል።

የትምህርት ሚኒስትርዲደኤታ ዶክተር ገረመው ሁሉቃ÷ የትምህርት አመራሩን አቅም በማሳደግ በትምህርት ቤቶች ውጤት ለማስመዝገብ በሚያስችል መልኩ ሪፎርሞቹ መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።

የስልጠናው ለውጥም ከንድፈ ሀሳብ በዘለለ በተግባር አመራሮቹ ትምህርት ቤታቸውን እና አካባቢያቸውን መሰረት በማድረግ የሚሰለጥኑበት መሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው ተነግሯል።

የተዘጋጁ ሞጁሎች የትምህርት ቤት አመራሮች እየሰሩ የሚማሩበት እየተማሩ የሚሰለጥኑበት በመሆኑ የትምህርት አመራሩን ሙያዊ ብቃት፣ ተወዳደሪነት እና ተነሳሽነት የሚጨምሩ መሆናቸውን ሚኒስትር ዲኤታው ገልፀዋል።

አዲስ የተዘጋጁት የስልጠና ማንዋሎች ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የመምህራን ኮሌጆች፣ የክልል ትምህርት ቢሮዎችና ከትምህርት ሚኒስቴር በተውጣጡ ባለሙያዎች እየተገመገሙ እና የማጠናከሪያ ሀሳቦች እየተሰበሰበ ይገኛል ነው የተባለው።

የስልጠና ማንዋሉ በዚህ ዓመት በተመረጡ አምስት ክልሎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ ከተደረጉ በኋላ በመላ ሀገሪቱ የሚተገበር መሆኑን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version