አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በኢትዮጵያ የተከናወነውን የፖለቲካ ለውጥ ሂደትና ቀጣይ አቅጣጫዎች የሚያመላክት መጽሐፍ ተመርቋል።
በእንግሊዝኛ ቋንቋ “Ethiopia in the wake of political reforms” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መፅሐፍ አራት ክፍሎችና 616 ገፆችን ይዟል።
በ20 ምሁራን የተዘጋጀው መፅሃፉ በአገሪቷ ባለፉት ሁለት ዓመታት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማኅበራዊ ጉዳዮች የተካሄደውን ለውጥ የዳሰሰ መሆኑ ተገልጿል።
ኅብረተሰቡ ስለ ለውጡ ያለውን ግንዛቤና የለውጡን ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችም አመላክቷል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው የመፅሃፉ ምረቃ ላይ የተገኙ ምሁራን፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ጋዜጠኞች በመፅሐፉ ዙሪያ ውይይት ማካሄዳቸውን ኢዜአ ዘግቧል ።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

