Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአውሮፓ ህብረት በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ሶስቱ ሀገራት በአፍሪካ ህብረት አሸማጋይነት እያደረጉት ላለው ድርድር ሙሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 14 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህዳሴው ግድብ ሙሌት ዙሪያ ኢትዮጵያ ግብፅና ሱዳን በወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር በደቡብ አፍሪካ አማካኝነት እያደረጉ ያሉትን ድርድር የአውሮፓ ህብረት እንደሚደግፍ ገለጸ።

ህብረቱ በመግለጫው ሶስቱ ሀገራት በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት ለችግራቸው ዕልባት ለመስጠት እየሄዱበት ያለውን መንገድ የምንደግፍበት እንጂ አላስፈላጊ ውጥረት የምንፈጥርበት ጊዜ አይደለም ብሏል።

ከ250 ሚሊየን ህዝብ በላይ በሚኖርበት በአባይ ተፋሰስ ቅድሚያ የሚሰጠው ሊደገፍ የሚገባውም ድርድር ብቻ ነው ብለዋል።

በመሆኑም ኢትዮጵያ ግብፅና ሱዳን በወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ደቡብ አፍሪካ አማካኝነት እየደረጉ ያሉትን ድርድር ህብረቱ እንደሚደግፍ የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ ጆሴፕ ቦሬል ገልፀዋል።

ግዜው እንዲህ ዓይነቱ ድርድር ለመደገፍ የምንነሳበት እንጂ አላስፈላጊ ውጥረት በቀጠናው እንዲፈጠር የምናደርግበት ጊዜ አይደለምም ነው ያሉት ።

ለዚህም የአውሮፓ ህብረት በደቡብ አፍሪካ አደራደሪነት ሶስቱ ሀገራት ልዩነታቸውን በውይይት ለመፍታት የሚያደርጉትን ጥረት ሙሉ በሙሉ ይደግፋል ሲሉ ገልጸዋል።

Exit mobile version