Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ የጀመረችውን የለውጥ ግስጋሴ ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር የሁሉም ሃላፊነት ነው -የሰላም ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ የጀመረችውን የለውጥ ግስጋሴ ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር የሁሉም ታሪካዊ ሃላፊነት መሆኑን የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ አቶ አለማየሁ እጅጉ ተናገሩ፡፡

የብሄራዊ ምክክር እና ሰላም ግንባታ አካል የሆነው የውይይት እና ተሳትፎ መድረክ ዛሬ በአዲስ አበባ ተከፍቷል፡፡

መድረኩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች የሚለዩበት እና የጋራ የሆኑ ጉዳዮች ይበልጥ ለማጠናከር መንገድ የሚጠርግ ነው ብለዋል ሚኒስትር ዲኤታው፡፡

እንዲሁም ያለ አድሎ፣ በቅንነት፣ በእኩልነት እና ዜጎችን ባከበረ መልኩ ማገልገል የዕለት ተዕለት የስራ አካል ማድረግ የሚያስችል የአስተሳሰብ ጥምረት ለመፍጠር ያለመ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በመድረኩ ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ የክልል፣ የዞን እንዲሁም የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

የውይይት መድረኩ ዛሬን ጨምሮ ለሶስት ቀናት የሚካሄድ መሆኑም ታውቋል፡፡

በዙፋን ካሳሁን

Exit mobile version