አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17 ቀን 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓትን ለማሻሻል የወጡ የትራፊክ ህጎችን የተላለፉ 15 ሺህ 8 37 አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል፡፡
ቅጣቱ ህግ በጣሱ፣ ከአቅም በላይ ትርፍ በጫኑ፣ ከታሪፍ በላይ ባስከፈሉ፣ ከተመደቡበት ርቀት በታች አቆራርጠው በጫኑ፣ ታፔላ ባለመስቀል እና ተያያዥ ጥፋቶችን በፈጸሙ አሽከርካሪዎች ላይ ነው ተብሏል፡፡
የትራፊክ ህግን በመጣስ በተጣለው ቅጣት ከ7 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት አስታውቋል፡፡
የትራንስፖርት አገልግሎቱን ለማሻሻል በተለይ ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ስርዓት ለማስያዝ የትራፊክ ህግ ጥሰት ቅጣት እንደሚጣልበት ጳጉሜን 2 ቀን 2012 ዓ.ም የወጣው ከፊል ማሻሻያ የተደረገበት መመሪያ ያመላክታል፡፡
በአዳነ አረጋ

