አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሠላም ወደ አማራ ክልል ለሚገቡ የትግራይ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ አባላት ዋስትና እንደሚሠጥ የአማራ ክልል አስታወቀ፡፡
የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ በፌስ ቡክ ገጻቸው እንዳስታወቁት በሠላም ወደ አማራ ክልል ለሚገቡ የትግራይ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ አባላት ዋስትና ይሰጣል፡፡
“ሀገርና ወገን ወዳድ የትግራይ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ ተገደህ እንደምትዋጋ እናውቃለን:: በሰላም ወደ አማራ ክልል ከገባህ ለህይወትህ ዋስትና እንደምንሰጥህ አውቀህ የሚጠበቅብህን አድርግ::” ብለዋል ርእሰ መስተዳድሩ፡፡
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

