Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሱዳን ዳርፉር የተሰማራው 24ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ ለተተኪው 25ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አስረከበ

አዲስ አበባ ፣ህዳር 3 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሱዳን ዳርፉር የተሰማራው 24ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ ግዳጁን አጠናቆ ለተተኪው 25ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አስረከበ ።
በወቅቱም የአስረካቢው ሻለቃ አዛዥ ኮሎኔል አድማሱ ተክሌ ÷ ምንም እንኳን የግዳጁ ባህሪ ውስብስብና አስቸጋሪ ቢሆንም ሻለቃው አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ ችሏል ብለዋል ፡፡
የተረካቢው ሻለቃ አዛዥ ኮሎኔል ተፈራ መላክ በበኩላቸው ÷ ከአስረካቢው ሻለቃ ያገኘናቸውን ተሞክሮዎች እንደ ግብአት በመጠቀምና ጠንክረን በመስራት ኢትዮጵያ በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ ያላትን ተፈላጊነትና መልካም ስም እናስጠብቃለን ማለታቸውን ከኢፌዲሪ የመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ፡፡
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
Exit mobile version