Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሰሜን አሜሪካና አውሮፓ የሚገኙ የኢትዮጵያ ሲቪክ ድርጅቶች የህግ የበላይነትን ለማስከበር በከሃዲው የህወሓት የጥፋት ቡድን ላይ የተጀመረውን ዘመቻ የአለም አቀፉ ማህበረስብ ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲይዝ ባለ ሶስት ገጽ ደብዳቤ አሰራጩ

አዲስ አበባ፣ህዳር 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ተቀማጭነታቸውን በሰሜን አሜሪካና አውሮፓ ያደረጉ የኢትዮጵያ ሲቪክ ድርጅቶች የኢትዮጵያ መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር በከሃዲው የህወሓት የጥፋት ቡድን ላይ የጀመረውን ዘመቻ የአለም አቀፉ ማህበረስብ ትክክለኛውን ግንዛቤ እንዲይዝ እና እንዲደግፍ ባለ ሶስት ገጽ ደብዳቤ አሰራጩ፡፡
ደብዳቤው ለተባበሩት መንግስታት፣ ለአፍሪካ ህብረት፣ ለአለም አቀፍ ሚዲያ ተቋማት እና ለልዩ ልዩ የአለም አቀፍ ተቋማት እንዲደረስ መደረጉ ታውቋል፡፡
ከሰሞኑ ህወሓት ከአለም አቀፍ የፕሮፖጋንዳ ማሽነሪ ፣ ከሌሎች ጽንፈኛ ሃይሎች፣ እንዲሁም ከባእዳን ጋዜጠኞችና ምሁራን ጋር በማበር በአለም አቀፍ ደረጃ በሚዲያዎች፣ በፓርላማ አባላት፣ በሶሻል ሚድያ የሚደረግ የተቀነባበረ ዘመቻ በኢትዮጵያ ውስጥ እየሆነ ያለውን፣ ግጭቱ መቼ፣ ለምን እና በምን ምክንያት የሚሉ ጉዳዮችን በሚመለከት በርካታ የሃስት ትርክቶች አሰራጭቷል፡፡
በተጨማሪም መንግስት ተገዶ የገባበት መሆኑ እውነታ ሆኖ ሳለ ትግራይን ለመውረር እንደሚደረግ ተደርጎ ለማቅረብ የተሄደበትን ውዥንብሮችና ውሸቶችን ለማጥራት በማሰብ ድርጅቶቹ በጋር ውይይት በማድረግ የተዘጋጀ ደብዳቤ ነው።
የዚህን ደብዳቤ ይዘት መነሻ በማድረግም በምትገኙባቸው ሀገሮች መንግስታት፣ ለጋዜጠኞች፣ ለፓርላማ አባላት፣ ለሲቪክ ተቋማት ፣ በተለይም ጽንፈኞቹና የህወሓት አሸባሪዎች የውጭ ተባባሪዎች ትኩረት ያደረጉባቸውና የተሳሳተ ግንዛቤ ያላቸውን፣ የተሳሳተ መግለጫ ላወጡ ልዩ ልዩ የመንግስትና ከመንግስት ውጭ የሚገኙ ተጽእኖ ፈጣሪዎች እንዲሁም ለሚዲያዎች በማድረስ ትብብር እንዲደረግ ጥሪ ቀርቧል፡፡
Exit mobile version