Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እና ኢቪድ ኮንስትራክሽን ለመከላከያ ሰራዊት 3 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ድጋፍ አደረጉ

 አዲስ አበባ ፣ህዳር 7 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እና ኢቪድ ኮንስትራክሽን ለሃገር መከላከያ ሰራዊት 3 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ድጋፍ አደረጉ።
የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በትግራይ የህግ ማስከበር ዘመቻ ላይ ለሚገኘው የሃገር መከላከያ ሰራዊት ያለውን አጋርነት ለመግለጽ 2 ሚሊየን ብር ድጋፍ በማድረግ ለመከላከያ ሚኒስቴር አስረክቧል።
ድጋፉን ያስረከቡት የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ጀማል የህወሓት ጁንታ ቡድን በሰራዊቱ ላይ የፈጸመውን አስነዋሪ ድርጊት አውግዘዋል።
በተያያዘም ኦቪድ ኮንስትራክሽን በህግ ማስከበር ዘመቻ ላይ ለሚገኘው ሰራዊት ግምታቸው 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የሆነ 30 ሰንጋዎችና 60 ሙክቶች ድጋፍ አድርጓል።
የኦቪድ ኮንስትራክሽ ባለቤትና ስራ አስኪያጅ አቶ ዮናስ ታደሰ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት ድርጅታቸው ለመከላከያ ሰራዊቱ ያለውን አጋርነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
የተደረገውን ድጋፍ የተረከቡት የመከላከያ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ማርታ ሉዊጂ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለሰራዊቱ ያለውን ድጋፍ እያሳየ መሆኑን ጠቁመው ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
Aa
Exit mobile version