አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ለመከላከያ ሰራዊት፣ ለአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ድጋፍ አደረጉ፡፡
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሰራተኞች ሀገርንና ህግን ለማስከበር ግንባር ለሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ 2 ሚሊየን 52 ሺህ 858 ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ድጋፉን ያደረጉት ከደመወዛቸው እስከ 100% ድረስ ተቀናሽ በማድረግ መሆኑን አብመድ ዘግቧል፡፡
ዩኒቨርሲቲው የሚያደርገው ድጋፍ እንደተጠበቀ ሆኖ መምህራንና ሰራተኞች በቀጣይም የአሸባሪው የወያኔ ቡድን ከሀገር እስከሚጠፋ ድረስ ከጸጥታ ኃይሉ ጎን በመሆን ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል።
በዩኒቨርሲቲው የሚገኙ የአስተዳደር ሰራተኞች እና መምህራን ሀገር የህልውና አደጋ ሲጋረጥባት ማንኛውንም እንቅስቃሴ በማድረግ ሀገርን የማዳን ተግባር እንደሚያከናወኑም ገልጸዋል፡፡

