Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል “ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ክብር እቆማለሁ” መርሃ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች “ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” መርሃ ግብሮች በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ተካሄደዋል።

በክልሉ በተካሄዱት የ”ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” መርሃ ግብሮች ላይ አመራሮች፣ የክልሉ የጸጥታ አካላት፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የመንግስት ሠራተኞች ተሳትፈዋል።

በዚህ መርሃ ግብርም ረፋድ 5 ሰዓት ከ30 ላይ ቀኝ እጃቸውን በግራ ደረታቸው ላይ በማስቀመጥ፣ ባንዲራውን ከፍ በማድረግ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ክብርና አጋርነት ማሳየታቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።።

Exit mobile version