Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ ከአረብ ሊግ ዋና ጸሀፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 8 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በግብጽ የኢትዮጵያ አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ ከዓረብ ሊግ ዋና ጸሀፊ አህመድ አባኡል ጊሂት ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም አምባሳደር ማርቆስ በኢትዮጵያ መንግስት የጀመረውን ህግና ህገ መንግስት የማስከበር ስራ በተመለከተ አብራርተዋል፡፡

የኢትዮጵያን እና የግብፅ ግንኙነትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንደሚሰሩ አምባሳደር ማርቆስ ለዋና ፀሀፊው ገልጸዋል ፡፡

የዓረብ ሊግ ዋና ጸሀፊ አህመድ አባኡል በበኩላቸው÷ አምባሳደር ማርቆስ በኢትዮጵያ እና በግብፅ መካከል የተጠናከረ ግንኙነት እንዲኖር ለማስቻል ያላቸውን ቁርጠኝነት አድንቀዋል ፡፡

ዋና ፀሀፊው አያይዘውም የኢትዮጵያ ሰላም ለአፍሪካ ቀንድ እና ለቀይ ባህር አካባቢ ደህንነት ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡

ከዚህ ባለፈም ዋና ጸሀፊው ከአምባሳደር ማርቆስ ተክሌ ጋር በቅንጅት ለመስራት መዘጋጀታቸውን ጠቁመው ÷ አምባሳደሩ ለዓላማቸው መሳካት የሚያደርጉትን ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኛ እንደሆኑ መናገራቸውን በግብጽ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version