አዲስ አበባ ፣ ህዳር 9 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በግብጽ የኢትዮጵያ አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ በግብፅ የዓረብ ሪፐብሊክ የእንግሊዝ አምባሳደር ከሆኑት ጂኦፍሬይ አዳምስ ጋር ተወያዩ ፡፡
በውይይታቸው ወቅት በሁለትዮሽ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም ሁለቱ አምባሳደሮች በጋራ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት መስማማታቸውን በግብጽ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

