Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በቻይና አንድ ህንፃ ላይ በደረሰ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደቡብ ምዕራብ ቻይና በአንድ ህንፃ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ስድስት ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተሰማ፡፡

ቃጠሎው የደረሰ በደቡብ ምዕራብ ቻይና ቾንግኪንግ ማዘጋጃ ቤት ፍሊንግ አውራጃ ውስጥ ነው።

አደጋው አንድ የመኖሪያ ህንፃ ባደረሰው የእሳት አደጋ ምክንያት የተፈጠረ ሲሆን፥ ቢያንስ ለስድስት ሰዎች ሕይወት ህልፈት ምክንያት ሆኗል ነው የተባለው፡፡

ሆኖም እሳቱን ከአንድ ሰዓት በኋላ በቁጥጥር ስር ማዋል የተቻለ ሲሆን፥ የእሳት አደጋው መንስኤ እየተጣራ ይገኛል።

ምንጭ፦ ሲጂቲኤን

Exit mobile version