Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከትግራይ ክልል ወደ ሱዳን በገቡ ኢትዮጵያውያን ዙሪያ ከሱዳን መንግስት ጋር በትብብር እየሰራን ነው- አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከትግራይ ክልል ወደ ሱዳን በገቡ ኢትዮጵያውያን ዙሪያ የኢትዮጵያ መንግስት ከሱዳን መንግስት ጋር በሁሉም መስክ ተባብሮ እየሰራ መሆኑን በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ገለፁ።
በሱዳን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ከስካይ ኒውስ የአረብኛ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል።
በዚህም መንግስት በትግራይ ክልል የጀመረው ሕግ የማስከበር እርምጃ ጥቂት ወንጀለኞችን ለህግ ለማቀረብ የሚደረግ ዘመቻ መሆኑን አስታውቅዋል።
ይህም ማንኛዉም መንግስት የሚያደርገዉ እንደሆነ የገለፁት አምባሳደሩ ማንም መንግስት ህግ እየተጣሰ ቁጭ ብሎ የሚያይበት ሁኔታ እንደሌለ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት እየወሰደ በሚገኘው እርምጃ ምክንያት ችግሩ አካባቢያዊ ሊሆን የሚችልበት እድል እንደሌለ ጠቅሰዋል።
በህግ ማስከበረ ሂደት ከቀያቸዉ ተፈናቀለው ወደ ሱዳን የገቡ ኢትዮጵያውያን በተለይም የምዕራቡ ትግራይ ክፍል ሙሉ በሙሉ ሰላም የተረጋገጠ በመሆኑ በቅርቡ ወደ ቀያቸው እንደሚመለሱ አረጋግጠዋል።
ከዚህ ጋር በተያየዘ ከሱዳን መንግስት ጋር በሁሉም መስከ በትብብር እየሰሩ መሆኑንም አምባሳደሩ አስገንዝበዋል።
Exit mobile version