Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በ80 ሚሊየን ብር የተገነባው የጋሻሞ ሆስፒታል ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ በጀረር ዞን የተገነባውን የጋሻሞ ሆስፒታል መርቀው ከፍተዋል።
ሆስፒታሉ በ80 ሚሊየን ብር የተገነባ ሲሆን÷ በዙሪያው ለሚገኙ 5 ወረዳዎች አገልግሎት እንደሚሰጥ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።
ሆስፒታሉ 60 በመቶ በሰው ኃይል እና በቁሳቁስ መደራጀቱን የገለፁት አቶ ሙስጠፌ በተለይ በክልሉ በወሊድ ወቅት የሚከሰት የእናቶች ሞትን ለመቀነስ ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
የሶማሌ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር ሸርማርኬ ሸሪፍ በበኩላቸው÷ የሆስፒታሉ ተገንብቶ ለአገልግሎት ብቁ መሆን ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ያለውን የክልሉን የቤተሰብ ምጣኔ ለመሻሻል ያግዛል ብለዋል።
ሆስፒታሉ በዙሪያው ለሚገኙ 800 ሺህ ለሚጠጉ የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ የተገነባ መሆኑም ታውቋል፡፡
አሁን ላይ በክልሉ 12 የሚጠጉ ሆስፒታሎች 1 ቢሊየን ብር በሚጠጋ በጀት የግንባታ፣ የማስፋፊያ እና የማሻሻያ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸው መገለፁን ከሶማሌ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክል፡፡
Exit mobile version