Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የብሔራዊ ጤና መረጃ ስርዓት አስተባባሪ ኮሚቴ በኢትዮጵያ የጤና መረጃ ላይ በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ውይይት አካሄደ

አዲስ አበባ ፣ህዳር 16 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ከመንግስትና ከአጋር ድርጅቶች የተዋቀረው የብሔራዊ ጤና መረጃ ስርዓት አስተባባሪ ኮሚቴ በኢትዮጵያ የጤና መረጃ አብዮት ላይ እስካሁን የተሰሩ ስራዎችን እንዲሁም የታዩ ክፍተቶች እና ተግዳሮቶች ዙሪያ ውይይት አካሄደ።
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ ÷በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመረጃ ጥራት እንዲሁም መረጃን በሁሉም ደረጃዎች መጠቀም የጤና ስርዓትን ለማሻሻል መሰረት ነው ብለዋል።
ዶክተር ሊያ አያይዘውም እነዚህን ቁልፍ ጉዳዮች ወደፊት ለማስኬድ የጤና መረጃ አስተዳደር ስርዓትን ለማጠናከር በውይይቱ ተስማምተናልም ነው ያሉት፡፡
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
Exit mobile version