አዲስ አበባ ፣ ህዳር 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሜካናይዜሽን እርሻ ለማስፋፋት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አምባሰል ንግድ ሥራዎች ድርጅት ጋር በመተባበር 5 ኮምባይነሮችን ለአርሶ አደሮች ማስረከቡን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡
ኮምባይነሮቹ በ30 70 ብድር ስምምነት መሠረት የተገዙ ናቸው ተብሏል።
እንዲገዙ ስምምነት ከተደረገላቸው 9 ኮምባይነሮች መካከል ዛሬ የአምስቱ ርክክብ የተፈፀመ ሲሆን ቀሪ አራት ኮምባይነሮች ደግሞ ወደብ ላይ እንደሚገኙ መነገሩን አብመድ ዘግቧል፡፡

