Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በጉጂ ዞን እጃቸውን ለሰጡና በቁጥጥር ስር ለዋሉ 405 የኦነግ ሸኔ አባላት የተሀድሶ ስልጠና እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በጉጂ ዞን እጃቸውን ለሰጡና በቁጥጥር ስር ለዋሉ 405 የኦነግ ሸኔ አባላት የተሀድሶ ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡

በቁጥጥር ስር የዋሉት የኦነግ ሸኔ አባላት በወንጀል ድርጊት ያልተሳተፉ እና በዞኑ ባሉ ወረዳዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ናቸው ተብሏል፡፡

ስልጠናው በሀገሪቷ ባለው ተጨባጭ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን የዞኑ የብልፅግና ፓርቲ አስታውቋል፡፡

ሰልጣኞቹ ስልጠናው ሲያራምዱ የነበረውን የተሳሳተ አመለካከት ትተው ወደ ሰላም፣ ልማትና ትክክለኛ ሰላማዊ ጎዳና እንዲመለሱ የሚረዳቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ስልጠናው ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ ይሆናል ነው የተባለው፡፡

Exit mobile version