አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ለቀጣይ አራት ወራት የሚቆይ የወጣቶች የአረንጓዴ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ስራ ተጀመረ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በከተማዋ ለቀጣይ አራት ወራት የሚቆየውን የወጣቶች የአረንጓዴ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ስራ መርሐግብርን አስጀምረዋል።
በመርሐግብሩ ማስጀመሪያ ምክትል ከንቲባዋ እንደገለፁት አዲስ አበባ ከተማ የጎብኚዎች መዳረሻ እንድትሆን እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴውን ለማሳደግ ውብ፣ ጽዱ እና ለኑሮ ምቹ መሆን ይኖርባታል ብለዋል።
በቀጣይ አራት ወራት በሚቆየው የወጣቶች የአረንጓዴ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከ28 ሺህ በላይ ሴቶች እና ወጣቶች በሣምንት ሁለት ቀናት እንደሚሳተፉም ተናግረዋል።
አዲስ አበባ ከተማ የአፍሪካ መዲናነቷን ፣ የቱሪዝም እና የዲፕሎማቲክ ማዕከልነቷን ለማስጠበቅ በሚደረገው ጥረት ሁሉም ነዋሪዎች ጽዳቷን በመጠበቅ ድርሻቸውን እንዲወጡ ምክትል ከንቲባዋ ጥሪ አቅርበዋል ።
በአዲስ አበባ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ እና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን አስተባባሪነት በሁሉም ክፍለ ከተሞች ሴቶች፣ ወጣቶች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በችግኝ እንክብካቤ በአረንጓዴ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ስራ የሚከናወን መሆኑን የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ገልጿል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

