አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ሞደርና የኮቪድ 19 ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቃድ ሰጠች፡፡
የሃገሪቱ የምግብ መድሃኒት እና ቁጥጥር ባለስልጣን የሞደርና ክትባት በአሜሪካ ሁለተኛው ክትባት ሆኖ ያገለግል ዘንድ እውቅና ሰጥቷል፡፡
ባለስልጣኑ ከሳምንት በፊት የፋይዘር/ባዮንቴክ ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቃድ ሰጥቶ ነበር፡፡
አሁን ላይም ዋሽንግተን 200 ሚሊየን የሞደርና ክትባት ለመግዛት ስምምነት ላይ የደረሰች ሲሆን ከዚህ ውስጥ 6 ሚሊየን የሚሆነው ክትባት ለስርጭት ዝግጁ መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡
የሞደርና ጥቅም ላይ መዋል በቫይረሱ በርካታ ዜጎቿን ላጣችው አሜሪካ ቫይረሱን ለመቆጣጠር ለምታደርገው ጥረት ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ክትባቱ 94 በመቶ ሰዎችን ከቫይረሱ የመከላከል አቅም እንዳለው ይነገርለታል፡፡
በአሜሪካ ከ17 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ሲኖርባቸው ከ313 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
ምንጭ፦ ቢቢሲ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

