አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 13 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ቡድን የአዋሽ ወልዲያ ሀራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክቱ በሚተገበርበት ወቅት የተካሄዱ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎችን ጎብኝቷል።
በዚህም ቡድኑ “የአዋሽ ወልዲያ ሀራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት” በባቡር ቴክኖሎጂና በሲቪል ስራዎች የእውቀት ሽግግር የተደረገበት መሆኑን ተመልክቷል።
ቡድኑ በተለይም በባቡር ቴክኖሎጂና በሲቪል ስራዎች የኢትዮጵያ ባለሙያዎች እውቀትን ከማሸጋገር አንፃር እና ስራውንም በመምራትና በመፈፀም የነበራቸውን ተሳትፎ በተመለከተ የተሰሩ አርአያ የሚሆኑ ስራዎችን መመልከቱን ገልጿል።
የባቡር ስራውን በትራንስፖርት ዘርፍ ለሃገሪቱ ከሚያደርገው አስተዋፅኦ በተጨማሪ ለሌሎች ቴክኖሎጂዎች ልማትም ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው ነው የተባለው።
ባቡሩን ተከትሎ የተዘረጋው ከ400 ኪሎ ሜትር በላይ የፋይበር ገመድ ለባቡሩ ከሚሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ የዲጂታል አገልግሎቶችን ለማስፋፋት ከፍተኛ ጥቅም እንደሚሰጥ ተገልጿል።
ከባቡሩ ጋር የተካተቱ ቴክኖሎጂዎች እና የአገልግሎት መስጫ ፋሲሊቲዎች ከሌሎች ተቋማት ጋር በተለይም ከዩኒቨርሲቲ፣ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች እና በአምራች ዘርፍ ከተሰማሩ ድርጅቶች ጋር በቴክኖሎጂው ዘርፍ በትስስር ለመስራት አመቺ ሁኔታዎችን ይፈጥራሉም ነው የተባለው።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲውን እየከለሰ የሚገኝ ሲሆን ይህ ፖሊሲ በቴክኖሎጂ ሽግግርና በተቋማት መካከል የሚደረጉ ትስስሮችን የሚያበረታታ መሆኑን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

