Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከወጪ ንግድ 1 ነጥብ 33 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 14፣ 2013(ኤፍቢሲ) የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ባለፉት አምስት ወራት ከወጪ ንግድ 1 ነጥብ 33 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱን አስታወቁ፡፡

ባለፉት አምስት ወራት 1 ነጥብ 41 ቢሊዮን ዶላር ከወጪ ንግድ ለማግኘት ታቃዶ 1 ነጥብ 33 ቢሊዮን ዶላር ገቢ የተገኘ ሲሆን የበጀት ዓመቱን የአምስት ወራት ዕቅዱ አፈፃፀም 94 በመቶ ማሳካት መቻሉን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

አፈጻጸሙም ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ224 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ጭማሪ ወይም የ20 በመቶ እድገት ማሳየቱን ገልጸዋል፡፡

በ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያ አምስት ወራት የማዕድን ዘርፉ ከዕቅድ በላይ 271 በመቶ ሲያስመዘግብ፣ የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ 93 በመቶ እንዲሁም ግብርናው 76 በመቶ ማሳካታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version