Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በደቡብ ክልል የከተማ ምግብ ዋስትና ኘሮግራም ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በደቡብ ክልል የከተማ ምግብ ዋስትና ኘሮግራም ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በኘሮግራሙ ላይ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በኢትዮጵያ የአለም ባንክ የከተማ ሴፍትኔት ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ደበበ ባሩድ የከተማ ልማት ኘሮግራም በአፍሪካ የመጀመሪያ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በፕሮግራሙ ለመሳተፍ ኢትዮጵያ ከአለም ባንክ ጋር ባደረገችው መግባባትና የተቀመጡ መስፈርቶችን በማሟላት የዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚ እንደሆነች ነው የተናገሩት።

በክልሉ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ኤጀንሲ ፕሮጀክት ተቀርፆ እና በጀት ተመድቦ ሰፊ ስራ እየተሰራ እንዳለም ጠቁመዋል።

ፕሮግራሙ በውይይት ዳብሮ በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ ማጠቃለያ ንግግር እንደሚጠናቀቅ ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version