Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ የከፍተኛ አመራሮች የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ የከፍተኛ አመራሮች የውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በውይይት መድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙ እንዲሁም የከተማው ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል ።

የመድረኩ አላማ የብልፅግና ፓርቲ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እና የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ የተወሰኑ ውሣኔዎችን ወደ ከተማዋ የአመራር መዋቅር ለማውረድ ታሳቢ ያደረገ ነው ተብሏል ።

በተጨማሪም ባለፉት አምስት ወራት በከተማዋ የልማት፣ የሠላምና የአገልግሎት አሰጣጥ ሁኔታ እና የተመዘገቡ ውጤቶች እንዲሁም ያጋጠሙ ፈተናዎችን ተቋቁሞ ውጤት ለማስመዝገብ በተደረገው ጥረት ዙሪያ ሰፊ ውይይት እየተካሄደበት ይገኛል ።

የመንግስትና የፓርቲ አመራርና መዋቅሩን ወደ ስራ ለማስገባት በኮንፈረንስ በስልጠናና በተግባር የተደረጉ ጥረቶችና የተመዘገቡ ውጤቶች ይገመገማሉ ተብሏል ።

በውይይት መድረኩ በቀጣይም ሀገራዊ ለውጡን ህዝባዊና ተቋማዊ መሠረት ለማስያዝ በሚያስችሉ የአመራር አቅጣጫዎች ላይ ከመግባባት ላይ ይደረሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version