አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 15 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አምባሳደር ዶክተር አዲስዓለም ባሌማ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበው ጉዳያቸው ታይቷል፡፡
በዚህም መርማሪ ፖሊስ በሰራቸው ስራዎች አምባሳደር አዲስ አለም ባሌማ ተልዕኮ ተቀብለው ሳይሆን በዋና ወንጀል አድራጊነት ሲንቀሳቀሱ እንደነበር ባገኘሁት ማስረጃ አረጋግጫለሁ ብሏል።
ተጠርጣሪው ኢትዮጵያን ከአፍሪካ እና ከተለያዩ ሀገራት ጋር ግንኙነቷን ለማሻከር እና ግንኙነቷን ለማቋረጥ ሲሰሩ እንደነበርም በማስረጃ ማረጋገጡን ፖሊስ ገልጿል።
ተጠርጣሪው በዋናነትም በምዕራብ ወለጋ ዞን ከሚገኘው የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን አመራሮግ ጋር በመገናኘት ከዶክተር ደብረጽን ገነብረሚካኤል ጋር በመሆን ለቡድኑ የገንዘብና የማቴሪያል ድጋፍ እንዲያገኙ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበርም መርማሪ ፖሊስ ገልጿል።
ከዚያም ባለፈ የአማራና የኦሮሞ ወጣቶችንም ለማጋጨት ከህወሓት አመራሮች ጋር ሲንቀሳቀሱ እንደነበር በቴክኒክ ምርመራ ማረጋገጡን ፖሊስ ለችሎቱ አስረድቷል።
ተጠርጣሪው ኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ወጣቶችን በመመልመል ፣በማደራጀት እና ትግራይ ክልል ወስደው በማሰልጠን በኦሮሚያ ክልልና በአዲስ አበባ ከተማ አመጽና ሁከት እንዲያስነሱ ያሰማሩ መሆኑንም በማስረጃ አረጋግጫለሁ ብሏል።
የተጠርጣሪው ቤት በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሲፈተሽም በርካታ የባንክ ደብተር አግኝተን እያጣራን እንደሚገኝም ፖሊስ ገልጿል።
ከተጠርጣሪው መኖሪያ ቤት የተገኙ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ለምርመራ መላኩንና በትግራይ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጸመው የወንጀል ድርጊት በአሰቃቂ ሁኔታ በርካታ ሰዎች የተገደሉበትን የጅምላ መቃብር ተቀበረበትና ጊዳት ደርሶባቸው ህክምና እየተሰጣቸው ያሉትን እንዲሁም ጉዳት የደረሰባቸውንና የወደሙ መሰረተ ልማትና የህዝብ ንብረትን መጠኑን አጣርቶ ለማቅረብና ሌሎች ቀሪ ስራዎች ለማከናወን የ14 ቀን ይሰጠኝ ሲል መርማሪ ፖሊስ ጠይቋል።
ተጠርጣሪው ዶክተር አዲስዓለም ከጠበቃቸው ጋር ቀርበው የምርመራ ጊዜ ሊሰጥ አይገባም ሲሉ ተከራክረዋል።
የዋስትና ጥያቄም አንስተዋል።
የሁለቱን ክርክር ያዳመጠው የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ ችሎትም ተጠርጣሪው በዋስ ቢወጡ ማስረጃ ሊያጠፉና ምርመራውን ሊያደናቅፉ ይችላሉ ሲል ከግምት ውስጥ አስገብቶ 13 ተጨማሪ ቀናትን ለመርማሪ ፖሊስ ፈቅዷል።
በታሪክ አዱኛ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለ

