አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውራምባ ታይምስ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ለ3ኛ ጊዜ ፍርድቤት ቀርቧል፡፡
ዳዊት ከበደ በተጠረጠረበት ወንጀል ፖሊስ የሰራውን የምርመራ ስራና ባሰባሰባው ማስረጃ ላይ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡
ተጠርጣሪው በሚዲያዎች ሲዘገብብኝ የፖሊስ ምርመራ ብቻ ነው ሲቀርብ የነበረው በሚል ቅሬታውን አቅርቧል፡፡
ዘገባው ሚዛናዊ መሆን ይገባዋል ሲልም ጠይቋል፡፡
እኔ ጋዜጠኛ ነኝ፣ ከወንጀሉ ጋር ግንኙነት የለኝም ሲል ተከራክሯል፡፡
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት መዝገቡን መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት ለታህሳስ 19 ቀን 2013 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ የመከላከያ አካዳሚክ ዲን ብርጋዴር ጄኔራል አሊጋዝ ገብሬን ጨምሮ የ4 መኮንኖች የምርመራ መዝገብ ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት ለፖሊስ 12 ተጨማሪ ቀናትን ፈቅዷል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

