Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል፤ 80 በመቶ ተማሪዎችም ወደ ቀጣዩ ክፍል መዛወራቸው ተገልጿል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል፤ 80 በመቶ ተማሪዎችም ወደ ቀጣዩ ክፍል መዛወራቸው የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ለክልላዊ ፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከልም 80 በመቶ ተማሪዎች ወደ ቀጣይ ክፍል የተዛወሩ ሲሆን ቢሮው የተሻለ ውጤትም መመዝገቡን ገልጿል፡፡

የፈተናው ውጤትም ለ10ሩም ክፍለ ከተማዎች በዛሬው ዕለት መሰራጨቱን ጠቅሷል፡፡

ቢሮው ተማሪዎች ከነገ ጀምሮ ውጤታቸውን በየትምህርት ቤቶቻችሁ መመልከት እንደሚችሉ ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ156 የመፈተኛ ጣቢያዎች 71 ሺህ 476 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸው አስታውቋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version