Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በኦሮሚያ ክልል ከ2 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው አልተመለሱም

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በኦሮሚያ ክልል ከ2 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው አለመመለሳቸው ተገለፀ።
የክልሉ ትምርህት ቢሮ ምክትል ሐላፊ አቶ ኤፍሬም ተሰማ እንደተናገሩት ÷በክልሉ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ትምህርት እንደገና የተጀመረ ቢሆንም ለማስተማር ከታቀደው 11 ነጥብ 5ሚሊየን ተማሪዎች ውስጥ ለመማር የተመዘገቡት 9 ነጥብ 5 ሚሊየን ብቻ ናቸው።
ከ2 ሚሊየን በላይ የሚሆኑትን ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ በቢሮው የሚገኝኙ የትምህርት ባለሙያዎች የንቅናቄ ስራ እስከታችኛው የህብረተሰብ ክፍል ድረስ አየሰሩ ይገኛሉ ነው ያሉት።
ሆኖም እስካሁን 84 በመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች ብቻ ናቸው ወደ ትምህርት ገበታቸው የተመለሱት ብለዋል ሃላፊው፡፡
በዚህም ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎች እንዲመለሱ ወላጆች፣ መምህራን እና ባለድርሻ አካላት በትጋት ሊሰሩ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
በምንይችል አዘዘው
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version