Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሾሙ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከታህሳስ 17 ቀን 2012 ዓም ጀምሮ የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው መሾማቸውን አስታውቋል።

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በኤርትራ የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉስልጣን አምባሳደር በመሆን በማገልገል ላይ ነበሩ።

አምባሳደር ሬድዋን በኤርትራ ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ሆነው ከመሾማቸው በፊት በአየርላንድ የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉስልጣን አምባሳደር በመሆን አገልግለዋል።

አምባሳደር ሬድዋን በተጨማሪም የኢፌዲሪ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትርነትን ጨምሮ በተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት የሃላፊነት ቦታዎች ማገልገላቸው ይታወቃል።

 

Exit mobile version