አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር 2ዐ ችግረኛ ህጻናት ተቀብሎ በቋሚነት ለመርዳት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ልደታ ክፍለ ከተማ ተቀበለ፡፡
ችግረኛ ህጻናቱን በይፋ የተረከቡት የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አሁን ካለው ሰፊ ችግር አንጻር የተረከብናቸው ህጻናት ቁጥር ትንሽ ቢሆንም በቀጣይ የምንቀበላቸው የህጻናት ቁጥር ለመጨመር እንሞክራለን ብለዋል፡፡
ህጻናቱን ለቁም ነገር ለማብቃት ጤና ሚኒስቴር የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣና እንደ ተቋም ይህንን አጋጣሚ ማግኘት ትልቅ እድል ነው ብለዋል፡፡
ህጻናቱን ለጤና ሚኒስቴር ያስረከቡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልደታ ክፍለ ከተማ የሴቶችና ህጻናት ጽህፈቤት ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉ ይርጋ በክፍለ ከተማው ከ252 በላይ ችግር ውስጥ የሚኖሩ ህጻናትን መለየታቸውን ተናግረው ጤና ሚኒስቴር ያደረገውን በጐ ተግባር ሌሎች ተቋማትም እንዲተገብሩት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ከዚህ ቀደም አቅመ ደካማ ሴቶችና ህጻናት ድጋፍ ሲደረግ እንደነበር የጠቆሙት ደግሞ የጤና ሚኒስቴር የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ ፋጡማ ሰይድ አሁን የተረከብናቸው ህጻናት በቋሚነት እንደራስ ልጅ ለመንከባከብ ቃል ገብተናል ብለዋል፡፡
ዶክተር ሊያ ታደሰ ለህፃናቱ የገና በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳቹ መልዕክትና ስጦታም ማበርከታቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳ
የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

