Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአዕምሮ ጤና ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጤና ሚኒስቴር የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት በአዕምሮ ጤና ዙሪያ የመጀመሪያ የሆነውን ሃገራዊ ውይይት አካሂዷል፡፡
በውይይቱ የጤና ሚኒስትር ደኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ የአዕምሮ ጤና በአገር አቀፍ ደረጃ ትልቅ ችግር ሆኖ ሳለ በበቂ ደረጃ ትኩረት ሳይሰጠው ኖሯል ብለዋል፡፡
በአዕምሮ ጤና ሕክምና አገልግሎት የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክረን እንሰራለን ያሉት ዶክተር ደረጄ በአምስት አመት የጤናው ዘርፍ የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ላይም የአዕምሮ ጤና ጉዳይ ተካቷል ብለዋል።
በመንግስት ደረጃም የአዕምሮ ጤና የማህበረሰቡ ትልቅ ችግር እየሆነ በመምጣቱ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ ተናግረዋል ።
የአዕምሮ ጤና ሕክምና አገልግሎት ላይ ተግዳሮቶች እንዳሉ የጠቆሙት የጤና ሚኒስቴር የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ ህይወት ሰለሞን ችግሩን ለመቅረፍ ጤና ሚኒስቴር ከባለድርሻዎች ጋር በመሆን የተጠናከረ ስረ መሰራት እንዳለበት ተናገረዋል።
ከዚህ ጎን ለጎን የአዕምሮ ጤና ሕክምና አገልግሎት ተቋማት ቁጥርን ለመጨመር እና ተደራሽነቱን ለማስፋት እየተሰራ መሆኑን ወይዘሮ ህይወት ሰለሞን መጠቆማቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳ
የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version